በዞኑ ሲሰጥ የቆየው የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና በሠላም መጠናቀቁን የሀዲያ ዞን ትምህርት መምሪያ ገለጸ

ከጥቅምት 29 እስከ ህዳር 2/2014 ዓ.ም ሲሰጥ የቆየው የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና በሠላም መጠናቀቁን የሀዲያ ዞን ትምህርት መምሪያ ገለጸ

በሀዲያ ዞን በ68 የፈተና ጣቢያዎች 17,255 ተማሪዎች ላለፉት አራት ተከታታይ ቀናት ሲሰጥ የቆነው የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና በሰላም መጠናቀቁን የዞን ትምህርት መምሪያ ኃላፊ ዶ/ር አበበ ሎለሞ ገልጸዋል።

የፈተና አሰጣጡ በሁለት ክላስተር ተከፍሎ በሁሉም የወረዳና የከተማ አስተዳደሮች ፍጹም ሰላማዊ በሆነ መልኩ መሰጠቱን ኃላፊው አስታውቀዋል።

የመምሪያው ኃላፊ ዶ/ር አበበ ሎላሞ በዞኑ የመልቀቂያ ፈተናው በሰላም እንዲጠናቀቅ አስተዋዕኦ ላበረከቱ ባለድርሻ አካላትን አመስግነዋል።

Image: